የቁጠባ አገልግሎቶች

መክሊት የተዳጊዎችና ወጣቶች የረዥም ጊዜ ተቀማጭ ሂሳብ

ታዳጊ ህፃናት ከለጋነት እድሜያቸው ጀምሮ በወላጆቻቸው አማካኝነት እንዲሁም ወደ ወጣትነት ሲሸጋገሩ ከራሳቸው ገቢ በየጊዜው የሚቆጥቡበት ከፍተኛ የቁጠባ ወለድ ክፍያ እንዲሁም የብድር አማራጮችን የሚያስገኝ የቁጠባ አይነት ነው፡፡ ወጣቶች በተማሪነት ዘመናቸው እንዲሁም ተቀጥረው በሚሰሩበት ወቅት ቆጥበው የራሳቸውን ሥራ ለመጀመር ፣ ለትምህርት እንዲሁም ለሌሎች ፍላጎቶቻቸው ብድር ማግኘት የሚችሉበትን አማራጮች ያካትታል

መክሊት የሴቶች ልዩ የቁጠባ ሂሳብ

ሴቶች ከፍተኛ የወለድ ክፍያ እያገኙ በረዥም ጊዜ ቁጠባ የራሳቸውን ሥራ ለመጀመር ወይም የሚሰሩትን ሥራ ለማስፋት አማራጭ የብድር አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸው የቁጠባ አይነት ነው፡፡ በተለይም በአረብ ሀገራት በስደት ለሚገኙ ሴት ወገኖቻችን በራሳቸው ወይም በቤተሰቦቻቸው አማካኝነት በተቋማችን የቁጠባ ሂሳብ ከፍተው በመቆጠብ ወደሃገር ቤት ሲመለሱ እስከ 60 በመቶ ብድር ከተቋማችን በማግኘት የራሳቸውን ሥራ ለመጀመር የሚያስችላቸው የቁጠባ አይነት ነው

መክሊት የአንጋፎች የጡረታ ዕቅድ

ይህ የቁጠባ ሂሳብ ከፍተኛ የወለድ ክፍያ የሚያስገኝ ሲሆን በሥራ ላይ የሚገኙ ጎልማሶች እንዲሁም ወደጡረታ ዘመናቸው የተቃረቡ አንጋፋዎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ እየቆጠቡ በጡረታ ዘመናቸው ተጨማሪ የገቢ ምንጭ የሚያገኙበት የቁጠባ አይነት ነው፡፡ በተጨማሪም ለህክምና ወጪያቸውና ከጡረታ በኋላ የራሳቸውን ሥራ መስራት ቢፈልጉ ከተቋማችን ብድር ማግኘት የሚችሉበትን አማራጭ ያካተተ ነው፡፡

መደበኛ የቁጠባ አገልግሎት

መደበኛ የቁጠባ አገልግሎት በፈቃደኝነት የቁጠባ ደብተር በማውጣት ደንበኛው የፈለገውን ያህል የገንዘብ መጠን የሚቆጥብበት የቁጠባ አይነት ነው

የሳጥን ቁጠባ አገልግሎት

ደንበኞች ከተቋማችን የቁጠባ ሳጥን በመውሰድ በየዕለቱ እንዲሁም በየሳምንቱ ከሚያገኙት ገቢ ላይ በእጃቸው በላው ሳጥን ውስጥ በመቆጠብ ወለድ የሚያገኙበት የቁጠባ አይነት ነው

ወለድ አልባ የቁጠባ ሂሳብ

ደንበኞች በፈቃደኝነት ያለወለድ ገንዘባቸውን በተቋማችን የሚያስቀምጡበት የቁጠባ አይነት ሲሆን ደንበኞች የሚያስቀምጡት ገንዘብ ለሚፈልጉት አላማ ብቻ እንዲውልላቸው የማዘዝ መብት አላቸው