ENG | AMH

መክሊት አነስተኛ የገንዘብ ተቋም አ.ማ. ገንዘብ ነክ እና ገንዘብ ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶችን በሃገራችን በከተማና በገጠር ለሚገኙ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ምርታማ ዜጎቸ በተለይም እድል ለተነፈጉ ሴቶች ለመስጠትበአዋጅ ቁጥር 40/96 በይፋ የተቋቋመ ድርጅት ነው ፡፡ የካቲት 9, 2000 ዓ.ም ፍቃድ አግኝቶ የተመዘገበና የተከፈለ ካፒታል 200 000 ብር በመያዝ ወደሥራ ገብቷል፡፡ መክሊት አነስተኛ የገንዘብ ተቋም አ.ማ. በአሁኑ ወቅት በአንድ ባለአክስዮን ድርጅት እና በ70 ግለሰብ ባለአክስዮኖች የሚተዳደር ነው፡፡ከአጠቃላይ ድርሻውም 75 በመቶ የሚሆነው ፕሮጃይኒስት በተሰኘ ሃገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተያዘ ነው፡:

በዚህ ወቅት ድርጅቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣በኦሮሚያና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልላዊ መንግስታት ውስጥ በመንቀሳቀስላይ ይገኛል፡፡ በስምንት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ እና በዘጠኝ ንዑስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አማካኘኝነት ከ 12,500 ለሚበልጡ ደንበኞቹ አገልግሎትን ይሰጣል፡፡ እነዚህ ስምንቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚገኙት በአዲስ አበባ፣አዳማ፣ደራ፣አርሲ ሮቤ፣ቡታጅራ፣መቂ፣ ወልቂጤ እና አቦምሳ ሲሆኑ የንዑስ ቅርንጫፍ ቢሮዎችን የከፈተባቸው ቦታዎች ደግሞ ኮልፌ፣ልደታ፣ሰበታ፣ሲሬ፣ጥቾ፣እንሴኖ፣እንድብር፣ጉንችሬ እና ስልጢ ናቸው፡፡

ራዕይ

መክሊት አነስተኛ የገንዘብ ተቋም በሃገራችን በድህነትየተጎዱዜጎች በተለይም እድል የተነፈጉ በከተማና በገጠር የሚገኙ ሴቶች ቀጣይ የሆነ የገንዘብ ምንጭ በማግኝታቸው የቀደመ ክብርና ሞገሳቸውተመልሶና በተለያየ ደረጃ ውሳኔ የመስጠት አቅማቸውጎልብቶ ለማየት የሚተጋ ድርጅት ነው፡፡

ተልዕኮ

ጥራቱን የጠበቀና የደንበኞችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ቀጣይ የገንዘብ ምንጭ በመሆን በድህነት ውስጥ የሚገኙ ምርታማ ዜጎቸን በተለይም እድል የተነፈጉ በከተማና በገጠር የሚገኙ ሴቶች ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ መሥራት፡፡

ማህበራዊ ግቦች

  • የመክሊት አነስተኛ የገንዘብ ተቋም አ.ማ ዒላማ የህብረተሰብ ክፍል በድህነት ውስጥ የሚገኙ ምርታማ ዜጎቸ በተለይም እድል የተነፈጉ በከተማና በገጠር የሚገኙ ሴቶች ናቸው
  • መክሊት አነስተኛ የገንዘብ ተቋም አ.ማ ጥራቱን የጠበቀና የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቀጣይ የገንዘብ ምንጭ በመሆን የደንበኞቹን ፍላጎት ያሟላል
  • ከደንበኞቹ እና ከቤተሰቦቻቸው የሚጠበቁ አወንታዊ ለውጦች
  • •ኢላማ የሆነው የህብረተሰብ ክፍል ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ደህንነታቸውን ማሻሻል

ዓላማ

  • ለጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተንቀሳቃሾች ፣ አነስተኛ የወር ገቢ ላላቸው፣ የጉልበት ሰራተኞችእና አርሶ አደሮች የብድር አገልግሎትን ከአዋጭ እና ሊተገበሩ ከሚችሉ ፕሮጀክቶች እንዲሁምከሞያዊ ድጋፍ ጋር በማጣመር ያቀርባል ፤
  • የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የገንዘብ ቁጠባንበማበረታታት ደንበኞቻችን ከአስከፊው የድህነት ሽክርክሪት በመውጣት የንግድ ድርጅታቸውን አቅም ከፍ እንዲያደርጉ ማገዝ፤
  • ተገቢ የሆኑየብድር ፣ የቁጠባ አገልግቶችን በቋሚነት እንዲያገኙ በማድረግእንዲሁም ሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶችን በመስጠት በድህነት ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሥራ ዕድሎችን መፍጠር
  • ገቢ የማግኛ እና የማስፊያ መንገዶችን በድህነት ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ማስተዋወቅ
  • በቂ ገቢን ሊያገኙ የሚችሉባቸውን የአቅም ግንባታ መርሐ-ግብሮችን ማዘጋጀት እና/ወይንም ማመቻቸት

ትኩረት የተደረገባቸው ደንበኞች

መክሊት አነስተኛ የገንዘብ ተቋም አ.ማ የተቋቋመው የጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተንቀሳቃሾች፣ የግል እና የመንግስት ድርጅት ሠራተኞች፣ የአርሶ አደሮችን እንዲሁም በማንኛውም ህጋው የገቢ ማግኛ እንቅስቃሴ ውስጥ የተሳተፉ አካላትን የገንዘብ ፍላጎት ለሟሟላት ነው ፡፡